በእጃችሁ ባለው ነገር ጥራት ያላቸውን ፊልሞች መስራት ይፈልጋሉ?

ይህ ባለ5 ክፍል ስልጠና ሞጁል በኪሳችሁ ያልተገደበ ቆንጆ ጥራት ያላቸውን ፊልሞች በመስራት የፊልምን ሃይል ለወንጌል እንድታውሉት ይረዳችኋል።

የቤተ ክርስቲያን መሪ ወይም ኢየሱስን የሚወድ ሰው ከሆኑ፣ ይህ ኮርስ እናንተ ከምታስቡት በላይ ብዙ ተመልካቾችን ለመንግሥቱ መማረክ የሚችል ጥራት ያለው የቪዲዮ ይዘት መፍጠር እንድትችሉ ኃይል ይሰጣችኋል።

ይህ ነፃ ኮርስ ለየት ያለ ፊልም ለመፍጠር የሚያስፈልጋችሁን መሠረታዊ ገጽታዎች እንደ ድርሰት (scriptwriting)፣ ፕሮዳክሽን (production)፣ድህረ-ፕሮዳክሽን (post-production) ፣ አርትዖት (editing)፣ የቅጂ መብት(copyright) እንዲሁም ስርጭትን (distribution)። ይህ ኮርስ እነዚህን እንዴት በትክክል ማድረግ እንደምትችሉ ያስተምራችኋል።

እስቲ ጠለቅ ብለን እንይ


ድርሰት (Scriptwriting)

ይህ ሞጁል በሚያስደንቅ ሁኔታ ልዩ የሆነ ድርሰት (Script) እንድትሰሩ እና በኦንላይን እንዲህም በእጃችሁ ያሉትን ሀብቶች ተጠቅማችሁ የተመልካቾችን ልብ የሚነካ አሳማኝ ፊልም ለመስራት ኃይል ይሰጣችኋል።

 

ፕሮዳክሽን (Production)

በዚህ ሞጁል ውስጥ ቪዲዮአችሁን እንዴት መቅረጽ መጀመር እንዳለባችሁ ትማራላችሁ። ቃራጻ ከመጀመራችሁ በፊት ማደራጀት ያለባችሁ አንዳንድ ነገሮች አሉ። ይህ ከፍል የቪዲዮ ቀራጻ አጠቃላይ ሂደቱን የበለጠ የተሳለጠ እና ቀልጣፋ ለማድረግ ይረዳችኋል።

 

ድህረ-ፕሮዳክሽን (Post-production)

ድህረ-ፕሮዳክሽን የሚያመለክተው ቀረጻችሁን ጨርሳችሁ ከወጣችሁ በኋላ ስለሚሆነውን ነገር ነው። ቀረጻችሁ ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ማከማቸት፣ የምስል እና የኦዲዮ ይዘትን ማስተካከል እና የድምጽ ተፅእኖዎችን (Sound effects) መጨመርን አካቶ እያንዳንዱን እርምጃ እንዴት በብቃት መተግበር እንደምትችሉ እናስተምራችኋለን።


አርትዖት (Editing)

አርትዖት (Editing) አንዳንድ ጊዜ በራሱ እንደ ፕሮጀክት ሊሰማን ይችላል! ይህ ሞጁል የእናንተን ዋና ስራ በተቻለ መጠን ያለምንም ህመም እንዴት ማስተካከል እንደምትችሉ ያሳያል። ልትጠቀሟቸው የምትችሉት ነጻ ሶፍትዌሮች እና አፕሊኬሽኖችን አካትተናል፤ ይህም በጀታችሁን የማይጎዳ ከፍተኛ ጥራት ያለው ቪዲዮ መስራት እንዲችሉ የራዳችኋል።

 

የቅጂ መብት (copyright)

ይህን ውስብስብ የሚመስለውን ርዕስ ከፋፍለን የቅጂ መብት ጋደቦችን እንዴት በተሻለ መንገድ ማስወገድ እንደምትችሉ እናሳያችኋለን! ይህ በእርግጥ ጌታን የሚያከብር ቪዲዮ ስትሰሩ ችላ ማለት የሚፈልጉት ነገር አይደለም!

 

ስርጭት (Distribution)

ለቪድዮአችን ማርኬቲንግ መስራት የማይቀር ነው። የታቀዱት ታዳሚዎች በጭራሽ የማያዩትን ቪዲዮ መስራት አይፈልጉም! ይህ ሞጁል መጀመሪያ ላይ ያሰባችሁትን ግብ እንዲመታ ቪዲዮአችሁን እንዴት ማሰራጨት እንደሚችሉ ያሳያችኋል!

Course Content


  መግቢያ
Available in days
days after you enroll
  ፊልም ለመስራት ዜሮ በጀት ኖሮዋችሁ ድርሰት (Script) እንዴት እንደሚጻፍ?
Available in days
days after you enroll
  የፕሮዳክሽን ደረጃ፡ ባላችሁ መሳሪያ ይዘታችሁን መቅረጽ
Available in days
days after you enroll
  ለቪዲዮ አርታኦት (Editing) የሚሆኑ ነጻ የድህረ-ፕሮዳክሽን መሳሪያዎች
Available in days
days after you enroll
  የቅጂ መብት መሰረታዊ መግቢያ
Available in days
days after you enroll
  ቪዲዮአችሁ መቀመጫው የትነው?
Available in days
days after you enroll